ባንተ ምሕረት
Bante Mihiret
አዜብ ኃይሉ · ሕያው አምላክ ነህ · 2024
Bante Mihiret is an Amharic mezmur (worship song) by Azeb Hailu, from the album Hiyaw Amlak Neh (2024).
ባንተ ምሕረት ባንተ ይቅርታ ነፍሴ እፎይ አለች አረፈች ጌታ (አረፈች ጌታ) ሰላም ተሰማኝ ተፅናናሁኝ (ተፅናናሁኝ) የኃጢአት እዳዬ ተሽሮልኝ (ተሽሮልኝ) የነፍሴ መድኃኒት ሆይ የእግዚአብሔር ልጅ ሆይ በመስቀል ላይ ያማጥክልኝ ለብቻህን አይደል ወይ (x2) ሌላ ማነው ከአንተ በስተቀር በእኔ ሕይወት ምሕረቱ የሚዘመር ሌላ ማነው ከአንተ በስተቀር በእኔ አንደበት ፍቅሩ የሚዘመር መፍትሄ ጠፍቶ ከሞት መዳኛ (ከሞት መዳኛ) ሁሉ ደካማ ሁሉ ኃጢአተኛ ተጨንቀን ሳለን በሞት ፍርሃት (በሞት ፍርሃት) ኢየሱስ መጣ የአምላክ ምሕረት (የአምላክ ምሕረት) የነፍሴ መድኃኒት ሆይ የእግዚአብሔር ልጅ ሆይ በመስቀል ላይ ያማጥክልኝ ለብቻህን አይደል ወይ ሌላ ማነው ከአንተ በስተቀር በእኔ ሕይወት ምሕረቱ የሚዘመር ሌላ ማነው ከአንተ በስተቀር በእኔ አንደበት ፍቅሩ የሚዘመር ዘምሪ ዘምሪ ነፍሴ ዘምሪ ደስ ይበልሽ ከዘላለም ሞት መዳኛ መድኃኒት ተወልዶልሽ (2) በጌታ በኢየሱስ ሞት ደግሞም በትንሳኤው ባመንሽ ጊዜ ፈትኖ አደረገሽ ሕያው (2) የነፍሴ መድኃኒት ሆይ የእግዚአብሔር ልጅ ሆይ በመስቀል ላይ ያማጥክልኝ ለብቻህን አይደል ወይ ሌላ ማነው ከአንተ በስተቀር በእኔ ሕይወት ምሕረቱ የሚዘመር ሌላ ማነው ከአንተ በስተቀር በእኔ አንደበት ፍቅሩ የሚዘመር


