Gubae

መኖር አልችልም

Menor ALchilim

አስቴር አበበ · ሃሌሉያ · 2024

Menor ALchilim is an Amharic mezmur (worship song) by Aster Abebe, from the album Hallelujah (2024).

የኔ ጌታ የኔ ውበት የኔ ፍቅር የኔ ናፍቆት የኔ ወዳጅ የኔ ውበት የኔ ፍቅር የኔ ናፍቆት መኖር አልችልም ያላንተ (2) እፈራለሁ ሁሉም ክድንድን ያለ ነው መኖር አልችልም ያላንተ (2) እፈራለሁ ሁሉም ጭልምልም ያለ ነው አሁንም እላለሁ ጥማኝ አሁንም እላለሁ ራበኝ አሁንም እላለሁ ናፍቀኝ አሁንም እላለሁ ጥማኝ አሁንም እላለሁ ራበኝ አሁንም እላለሁ ናፍቀኝ በማንነትህ ልክ የረሃቤ ቁመቱ ይላቅ ከከበበኝ አይስረቅ እይታዬን ዘልቆ ላያዘልቀኝ ከጎደለኝ ነገር ከምለው ይህ ቀረ ይሁንልኝ ረሃቤ ለአንተ ያጋደለ አሁንም እላለሁ ጥማኝ አሁንም እላለሁ ራበኝ አሁንም እላለሁ ናፍቀኝ አሁንም እላለሁ ጥማኝ አሁንም እላለሁ ራበኝ አሁንም እላለሁ ናፍቀኝ በማንነትህ ልክ አንተን ማጣት ነው ብቸኝነት መጸለይ ማቆም ነው ድርቀት መንፈስህን መተው ነው ክስረት ውሎ ማደር አንተ በሌለህበት ቃልህን መርሳት ነው ጎዶሎነት ሳይሰሙህ መውጣት ነው ዙረት ያለ ድምጽህ ማውራት ነው ቅዠት ውሎ ማደር አንተ በሌለህበት መኖር አልችልም ያላንተ (2) እፈራለሁ ሁሉም ክድንድን ያለ ነው መኖር አልችልም ያላንተ (2) እፈራለሁ ሁሉም ጭልምልም ያለ ነው አንተን ተከትዬ ቤቴ ወና ይቅር ከአፈር የሆነው ይቅርብኝ በጅምር በአንተ ብቻ ልመር ላጊጥ በሃሳብህ ይልቀቀኝ የምድሩ ሳበኝ በፈቃድህ አሁንም እላለሁ ጥማኝ አሁንም እላለሁ ራበኝ አሁንም እላለሁ ናፍቀኝ አሁንም እላለሁ ጥማኝ አሁንም እላለሁ ራበኝ አሁንም እላለሁ ናፍቀኝ በማንነትህ ልክ በተጨመረልኝ ዕድሜ በተቀጠሉልኝ ቀናት ነፍሴን ዝም ጸጥ አሰኝቼ ከጌታ ውጭ ላልሰጣት ነጥቄአት ከሌላው ጎዳና ትዋል ኮቴህ በሚረግጥበት ልቤን እንዲህ አስፋልኝ እና ላጊጥ በፈቃድህ ውበት ልመረቅ በእጆችህ ለማዶው ሽልማት ፍለጋህ እንድከተል ጸጋህን ስጠኝ በብዛት ትሁን ነፍሴ እንዳልካት ደስታህ ሃይሌ ነው የሰማዩን ፈቃድህን በምድር ስኖረው አሁንም እላለሁ ጥማኝ አሁንም እላለሁ ራበኝ አሁንም እላለሁ ናፍቀኝ አሁንም እላለሁ ጥማኝ አሁንም እላለሁ ራበኝ አሁንም እላለሁ ናፍቀኝ በማንነትህ ልክ

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play

More songs by Aster Abebe

See all 37 songs by Aster Abebe