Gubae

እዩልኝ

Eyulign

አስቴር አበበ · ሃሌሉያ · 2024

Eyulign is an Amharic mezmur (worship song) by Aster Abebe, from the album Hallelujah (2024).

እዩልኝ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ /3 ላውራው ልዘምረው ልናገር ልተርከው ልጥራው ልደጋግመው ልመርኮዝ ልደገፈው ስሙ ከፊደል ያለፈ ነው ስሙ ከአንድ ቃል ያለፈ ነው ስሙ ከስሞች ያለፈ ነው ስሙ ከምለው ያለፈ ነው ስምህን ስጠራው ጥሜ ይረካልኛል ስምህን ስጠራው ከረሃቤ እጠግባለሁኝ/፪ ለዚህ ነው ሲነጋም ኢየሱስ የምለው ለዚህ ነው በቀትር ኢየሱስ የምለው ለዚህ ነው ሲመሽም ኢየሱስ የምለው ለዚህ ነው በሌሊት ኢየሱስ የምለው በምን አጎደልከኝ መች ጠናሁ የሰው ደጅ ከጫፍ ጫፍ ሙላት የምትደላ የምትመች ሰው እንኳን የሚያልፈውን ይኼ አለኝ ይላል አንድ ሁለት ሶስት ብሎ ያስቆጥራል የማታልቅ የማታልፍ የማትደክም ትምክህቴ የማልቀይርህ መዝሙር እስካለሁ በህይወቴ ለልጅ ልጅ ትምህርት ርስትም ያለኸኝ ለሚያዩኝ ሁሉ እዩልኝ የሚያስብለኝ እዩልኝ እዩልኝ ደግነቱን እዩልኝ እዩልኝ እዩልኝ ምህረቱን እዩልኝ እዩልኝ እዩልኝ ደግነቱን እዩልኝ እዩልኝ እዩልኝ ምህረቱን እዩልኝ ከማይደረስበት ከቅድስናው ጥግ በሞቱ አድርሶኝ ጸድቀሻል አለኝ እዩልኝ ካለሁበት ሸለቆ ህያው ቃሉን ልኮ ዳግም ሰው አርጎኝ አንቺ ብርቱ አለኝ እዩልኝ እዩልኝ እዩልኝ ደግነቱን እዩልኝ እዩልኝ እዩልኝ ምህረቱን እዩልኝ

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play

More songs by Aster Abebe

See all 37 songs by Aster Abebe