Gubae

ምኔ ደስ አሰኝቶህ

Mene Des Asegntoh

አስፋው መለሰ · በጅምር አይቀርም

Mene Des Asegntoh is an Amharic mezmur (worship song) by Asfaw Melese, from the album Bejmr Aykerm.

ስርቅህ እየቀረብከኝ ስጠላህ እየወደድከኝ ምኔ ደስ አሰኝቶህ ነው ከኔ ጋር ወዳጅ የሆንከው/2 ምስኪኑን ታናሽ ሰው ኧረ እንዴት ውደድከኝ እንዳገለግልህ እኔን የመረጥከኝ አሉ እኮ ጌታ ሆይ ከኔ የሚበልጡ በሰው አይን የሞሉ ተመርጠው የኖሩ ምኔ ደስ አሰኝቶህ ነው ከኔ ጋር ወዳጅ የሆንከው/2 ብዙዋች እያሉ ከኔ የተሻሉ ብዙ ዝና ያላቸው አንቱ የተባሉ ምኔ ደስ አሰኘህ እንዲ የወደድከኝ እኔን ስትጠራ ወዳጅ ልትሆነኝ ምኔ ደስ አሰኝቶህ ነው ከኔ ጋር ወዳጅ የሆንከው/2 ምንድን ነው ምኪያቱ እንዲ ለመውደድህ በፀጋህ አንስተህ ምስኪኑን ማክበርህ ሰው የረሳውን ሰው ልትቀባው መጥራትህ እኔስ አስገረመኝ ጌታ አሰራርህ ምኔ ደስ አሰኝቶህ ነው ከኔ ጋር ወዳጅ የሆንከው/2 መጀመሪያም መጨረሻዬ እየሱስ ነው የኔ ምርጫዬ ከሱ ሌላ አልመኝም እንደ ጌታ ማንም አይሆነኝም ሰው ያረገኝን ጌታ አልክደውም ያደረገልኝን አልረሳውም የጠራኝን ጌታ ጌታ አልክደውም ያደረገልኝን አልረሳውም ስርቅህ እየቀረብከኝ ስጠላህ እየወደድከኝ ምኔ ደስ አሰኝቶህ ነው ከኔ ጋር ወዳጅ የሆንከው/2

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play

More songs by Asfaw Melese

See all 16 songs by Asfaw Melese