Gubae

ከልጅነቴ ጀምሮ

Keljnete Jemro

አስፋው መለሰ · በጅምር አይቀርም

Keljnete Jemro is an Amharic mezmur (worship song) by Asfaw Melese, from the album Bejmr Aykerm.

ከልጅነቴ ጀምሮ ገና ከሕጻንነት ያኔ የተሸከመኝ ያ ሰፊ ትከሻህ ዛሬም አልሰለቸኝ/2 በእድሜ ቀናቶቼ ሃዘን እንዳይገዛኝ ምስጋናን ዝማሬን ለእኔ ሰጠህኝ ትዝታዬ ሆነህ ምሕረትህ ለኔ ከእጅህ አልጣልከኝም ዛሬም ቢሆን ያኔ/2 ከልጅነቴ ጀምሮ ገና ከሕጻንነት ያኔ የተሸከመኝ ያ ሰፊ ትከሻህ ዛሬም አልሰለቸኝ/2 ከዘመናት በፊት ከእሩቅ ያወቅኅኝ ገና ሳልፈጠር ዛሬን ያየህልኝ ለዚያ ለጠላቴ በክፉ ላሰበኝ አሳልፈህ ለሞት መች እኔን ሰጠሀኝ/2 ከልጅነቴ ጀምሮ ገና ከሕጻንነት ያኔ የተሸከመኝ ያ ሰፊ ትከሻህ ዛሬም አልሰለቸኝ/2 ስቀመጥ ስነሳ ሲጨልም ሲነጋ ላፍታ ሳትለየኝ ሆነህ ከእኔ ጋር እንደ አይንህ ብሌን ተጠነከክልኝ ማንም እንዳይነካኝ ትእዛዝህ ወጣልኝ/2 ከልጅነቴ ጀምሮ ገና ከሕጻንነት ያኔ የተሸከመኝ ያ ሰፊ ትከሻህ ዛሬም አልሰለቸኝ/2 በደሌ ከፍ ብሎ ሳለ ምሕረትህ በኔ ላይ ገነነ እኔ ነኝ እግዚአብሔር የረዳኝ ከትቢያ ካመድ ላይ ያነሳኝ እኔ ነኝ ጌታ የራራልኝ እኔ ነኝ ጌታ ሰው ያረገኝ እኔ ነኝ ይቅር የተባልኩኝ ከልጅነቴ ጀምሮ ገና ከሕጻንነት ያኔ የተሸከመኝ ያ ሰፊ ትከሻህ ዛሬም አልሰለቸኝ/2

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play

More songs by Asfaw Melese

See all 16 songs by Asfaw Melese