Gubae

ቆጠርከኝ

Qoterkegn

ዮሴፍ አያሌው · ስራዬን የሰራህልኝ

Qoterkegn is an Amharic mezmur (worship song) by Yoseph Ayalew, from the album Serayien Yeserahelegn.

አዝ፦ ቆጠርከኝ ፡ እንደ ፡ ባለማዕረግ ሳልለፋ ፡ ምንም ፡ ሳላደርግ ምህረትህ ፡ በዝቶልኝ ፡ በላዬ ኧረ ፡ ደግ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ ጌታዬ ልናገር ፡ እኔስ ፡ ቸርነትህን አላውቅም ፡ ክፉ ፡ መሆንህን (፪x) እኔማ ፡ ይገርመኛል ፡ ሁልጊዜ ፡ ይደንቀኛል እኔማ ፡ ይገርመኛል ፡ ሳስበው ፡ ይደንቀኛል ሹመት ፡ ሆኖልኝ ፡ ነው ፡ ከዓርያም ፡ የተወሰነ ማንም ፡ የማይቀያይረው ፡ ከላይ ፡ የሆነ ልጄ ፡ ነህ ፡ ብሎኛል ፡ ምን ፡ ልበል ፡ ይህ ፡ ማዕረጌ ፡ ነው ውስጤን ፡ መደነቅ ፡ ሞልቶታል ፡ ለእኔ ፡ በሆነው እኔማ ፡ ይገርመኛል ፡ ሁልጊዜ ፡ ይደንቀኛል እኔማ ፡ ይገርመኛል ፡ ሳስበው ፡ ይደንቀኛል አዝ፦ ቆጠርከኝ ፡ እንደ ፡ ባለማዕረግ ሳልለፋ ፡ ምንም ፡ ሳላደርግ ምህረትህ ፡ በዝቶልኝ ፡ በላዬ ኧረ ፡ ደግ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ ጌታዬ ልናገር ፡ እኔስ ፡ ቸርነትህን አላውቅም ፡ ክፉ ፡ መሆንህን በህልሜ ፡ በእውኔ ፡ አስቤ ፡ የማላውቀውን ብዙ ፡ አድርገህልኛል ፡ ያልጠበኩትን ልዘምር ፡ በገናዬን ፡ ላንሳ ፡ ቅኔን ፡ ልደርድር ግሩምና ፡ ድንቅ ፡ የሆነውን ፡ ስራህን ፡ ልናገር እኔማ ፡ ይገርመኛል ፡ ሁልጊዜ ፡ ይደንቀኛል እኔማ ፡ ይገርመኛል ፡ ሳስበው ፡ ይደንቀኛል አዝ፦ ቆጠርከኝ ፡ እንደ ፡ ባለማዕረግ ሳልለፋ ፡ ምንም ፡ ሳላደርግ ምህረትህ ፡ በዝቶልኝ ፡ በላዬ ኧረ ፡ ደግ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ ጌታዬ ልናገር ፡ እኔስ ፡ ቸርነትህን አላውቅም ፡ ክፉ ፡ መሆንህን አይቆጠር ፡ እንዲሁ ፡ አይባል ፡ ቸርነትህ የማይለወጠው ፡ ፍቅርህ ፡ የአባትነትህ ኧረ ፡ እንዴት ፡ ብዬ ፡ እገልጸዋለው ፡ ያረክልኝን ከቁጥር ፡ በላይ ፡ የበዛው ፡ የዋልክልኝን እኔማ ፡ ይገርመኛል ፡ ሁልጊዜ ፡ ይደንቀኛል እኔማ ፡ ይገርመኛል ፡ ሳስበው ፡ ይደንቀኛል አዝ፦ ቆጠርከኝ ፡ እንደ ፡ ባለማዕረግ ሳልለፋ ፡ ምንም ፡ ሳላደርግ ምህረትህ ፡ በዝቶልኝ ፡ በላዬ ኧረ ፡ ደግ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ ጌታዬ ልናገር ፡ እኔስ ፡ ቸርነትህን አላውቅም ፡ ክፉ ፡ መሆንህን

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play

More songs by Yoseph Ayalew

See all 9 songs by Yoseph Ayalew