Gubae

ክብሬ

Kibre

ዮሐንስ በላይ · ላድንቅህ

Kibre is an Amharic mezmur (worship song) by Yohannes Belay, from the album Ladenekeh.

ባዶነቴ ባንተ ሲሞላ ምን ይታሰበኛል ከማመስገን ሌላ ካንተ እየተቀበልኩ ላንተ እሰጣለው ደግሜ ደግሜ እባርክሃለው ክብሬ ልዘምርልህ/2 እየሱስ ልዘምርልህ/2 ፊትህን እንድሻ ክንዴ በረታልኝ ማለዳ ማለዳ እየፈሰስክልኝ የህይወት ትርጉሙ ባንተ ተፈታልኝ ከእግርህ ስር ቅጭ ብዬ አባት ሆነህልኝ ክንዴም አይታጠፍ ጉልበቴም አይዝል ክፍታን ትቼ አላይም ቁልቁል መላው እኔነቴ የተወረሰበት መንፈስ ቅዱስ አለኝ የምበረታበት ክብሬ ልዘምርልህ/2 እየሱስ ልዘምርልህ/2 ባዶነቴ ባንተ ሲሞላ ምን ይታሰበኛል ከማመስገን ሌላ ካንተ እየተቀበልኩ ላንተ እሰጣለው ደግሜ ደግሜ እባርክሃለው ክብሬ ልዘምርልህ/2 እየሱስ ልዘምርልህ/2 የህይወት ወጣ ገባ ዳገት ቁልቁለቱ ግራ እንዳይገባኝ ግለት ትኩሳቱ አላይ ወደግራ አላይ የቀኜን አንተኑ ሰማለው ውስጤ ያለውን ክንዴም አይታጠፍ ጉልበቴም አይዝል ክፍታን ትቼ አላይም ቁልቁል መላው እኔነቴ የተወረሰበት መንፈስ ቅዱስ አለኝ የምበረታበት ክብሬ ልዘምርልህ/2 እየሱስ ልዘምርልህ/2 ክብሬ/3 ክብሬ ነህ ሞገሴ

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play

More songs by Yohannes Belay

See all 24 songs by Yohannes Belay