Gubae

ተስፋዬ

Tesfayie

መስፍን ጉቱ · እንዲሁ በዋዛ · 2005

Tesfayie is an Amharic mezmur (worship song) by Mesfin Gutu, from the album Endihu Bewaza (2005).

ተስፋዬ ነህ አንተ ማረፊያዬ አንተ መታመንስ አንተ ኦ መመኪያ ነህ አንተ መመኪያዬ (፰x) ተስፋዬ አንተው ነህ ንጉሤ አንተው ነህ አምላኬ አንተው ነህ ወዳጄ አንተው ነህ የሚሳንህ የለም ንገሥ የሚያቅትህ የለም ንገሥ የሚሳንህ የለም ክበር የሚያቅትህ የለም ክበር በበረሃ ጋሻ ለተጠማ እርካታ ስትሆን አየሁህ የሱስ የእኔ ጌታ ጀርባህን ለደካማ ለበረታው ፊትህን ሰጥተህ አታደላም ሥምህ ብሩክ ይሁን (፭x) ለታላቅነትህ እቀኛለሁ ለጌትነትህም እሰግዳለሁ (፫x) ኢየሱስ ጌታ ነህ (፫x) የምስኪኑን ጥሪ ጩኸት ትሰማለህ በባዕድ ምድር ላይ አባት ትሆናለህ የተገፋን ማንሳት ማክበር ልማድህ ነው በሠማይ በምድር እንዳንተ ያለ ማነው (፬x) ለታላቅነትህ እቀኛለሁ ለጌትነትህም እሰግዳለሁ ፫x) ኢየሱስ ጌታ ነህ (፫x) ተስፋዬ ነህ አንተ ማረፊያዬ አንተ መታመንስ አንተ ኦ መመኪያ ነህ አንተ መመኪያዬ (፰x)

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play

More songs by Mesfin Gutu

See all 57 songs by Mesfin Gutu