Gubae

የሚጤስ ጧፌን አላጠፋም

Yemitesewen Tuafien Alatefam

ኤልያስ አብጤ · የሚጤስ ጧፌን አላጠፋም

Yemitesewen Tuafien Alatefam is an Amharic mezmur (worship song) by Elias Abte, from the album Yemitesewen Tuafien Alatefam.

የሚጤስ ፡ ጧፌን ፡ አላጠፋህም ቅጥቅጥ ፡ ሸምበቆዬን ፡ ከቶ ፡ አልሰበርክም ምሕረትህ ፡ በእኔ ፡ እጀጉን ፡ በዝቷል የማዳን ፡ ክንድህን ፡ ዓይኔ ፡ አይቶታል ክበር ፡ ተመስገን (፫) ዘላለም እንዳንተ ፡ ያለ ፡ የለም(፪) (፪x) 1)ቅጥቅጥ ሸንበቆን ጌታ የት ተሰብራለህ የሚጠሰውንስም ጧፍ መች ታጠፋለህ በሕይወት ታኖራለህ እንጂ ከቶ አትሰብርም ይህ ነው ሥራህ ጌታ ክበር ለዘለዓለም እጅግ በደሌ በዝቶ የተዋረድኩ ዓይኔ ባንተ ተከፍቶ ጽድቅን አየሁ ሕይወትን ይዘህ ጌታ መጣህ ወደኔ ለነፍሴ ቤዛ ሆንክ ክበር መድሃኔ አዝ፦ 2)እስከ ቀራንዮ ድረስ ጉድ ተሸክመህ ነብሴ በነብስህ ሲዋጅ ታሪክ ተፈፀመ የመዳኔ ምልክት ያኔ ታተመ የሰበረኝ ሀጥያቴ ጉልበቱ አከተመ ፍቅርህ እስከሞት ለኔ የበረታ ነው ከጥፋት ጉድጓድ ደርሶ ነብሴን አዳነው በኔ መቃብር ገብተህ ህይወት ሆነሀል የሚጤሰውን ጧፌን ጌታ አብርተሀል አዝ 3)38 አመት እግሬን አጥቼ በቤተ ሳይዳ ደጃፍ በዋዛ ተኝቼ ሰው እንደማይቀርበኝም ባይንህ አየኸኝ እጆቼን ይዘህ ጌታ በእግሬ አቆምከኝ እንኳን አልጋ ልሸከም መሄድ የማልችል ፍፁም የተሳሰርኩኝ ሽባ ነበርኩኝ ታምራትህን በህይወቴ አሳየኸኝ ሌላ ምን እላለሁኝ ክበር ተመስገን አዝ 4)ወደ ባሪያህ ሕዝቂያስ ዓይንህን መልሰህ በዕድሜው ላይ 15 ዓመት ጨምረህ የፈሰሰውን ዕንባ ከዓይኖቹ አበስከው በሕይወት እንዲኖር የሱስ ፈወስከው የሕዝቅያስስ ታሪክ የሕዝቅያስ ነው ለኔ ያደረክልኝ እጅግ ድንቅ ነው በነፍስም በስጋዬም ሙት የነበርኩኝ በቀራኒዮ ፍቅርህ በሕይወት ኑር አልከኝ

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play

More songs by Elias Abte

See all 10 songs by Elias Abte