Gubae

እንደገና

Endegena

ዳንኤል አምደሚካኤል · በአንተ ብርታት · 1997

Endegena is an Amharic mezmur (worship song) by Daniel Amdemichael, from the album Beante Birtat (1997).

አዝ፦ ኢየሱስ በጊዜው ደረሰልኝ እርሱ አይቶ መች ጨከነብኝ ዳግም ተስፋዬን አደሰው እንባዬን ካይኔ አበሰው አምላኬ ታሪኬን ለዋወጠው እንደገና እንደገና እንደገና እንደገና አቆመኝ /(፪x) የኤርትራ ባህር በፊቴ እኔን ሊውጥ አፍጥጦ የጠላቴ ጦር ከኋላ ሰይፉን መዞብኝ መጥቶ ተስፋ ቆርጬ ስጨነቅ ጌታ ድንቅ አደረገ የኤርትራን ባህር ከፍሎ እኔን በዚያ አሻገረ አዝ፦ ኢየሱስ በጊዜው ደረሰልኝ በመንገዴ ላይ የቆመ ታላቅ ግዙፍ ተራራ ቢገፉት የማይገፋ በሚያማርር መከራ ተሻግሮ ማለፍ አቅቶኝ ኃይሌም ከውስጤ አልቆ ኢየሱስ ከፊቴ አራቀው ሙቱን ተስፋዬን አደሰው አዝ፦ ኢየሱስ በጊዜው ደረሰልኝ የሕይወት ዘመኔ መንምኖ ሞትም ዙሪያዬን ከቦኝ ቀኔን ስጠብቅ ባልጋ ላይ ሕመም በጣም ጸንቶብኝ እጅግ ቆዝሜ ሳነባ ደረሰልኝ አባባ አዋጅን በአዋጅ ሻረ ሕይወትን ለኔ አበሰረ አዝ፦ ኢየሱስ በጊዜው ደረሰልኝ ሃብቴ ንብረቴ ሁሉ አልቆ ዘመድ አዝማድም ርቆኝ ከቁስሌ የተነሳ ሰው እጅጉን ተፀይፎኝ ሁሉን ቻይ የሆነ እግዚአብሔር እንደገና አሰበኝ ሕይወቴን አረሰረሰ ዳግም ምርኮዬን መለሰ አዝ፦ ኢየሱስ በጊዜው ደረሰልኝ እርሱ አይቶ መች ጨከነብኝ ዳግም ተስፋዬን አደሰው እንባዬን ካይኔ አበሰው አምላኬ ታሪኬን ለዋወጠው እንደገና እንደገና እንደገና እንደገና አቆመኝ /(፪x)

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play

More songs by Daniel Amdemichael

See all 64 songs by Daniel Amdemichael