Gubae

አይደለህም እንደሰው

Aydelehem Endesew

ዳግማዊ ጥላሁን · ሌላ ሌላ ሌላ · 2007

Aydelehem Endesew is an Amharic mezmur (worship song) by Dagmawi Tilahun, from the album Liela Liela Liela (2007).

አይደለህም እንደሰው አይደለህም ጌታዬ አይደለህም እንደሰው አይደለህም አምላኬ አንተ ሊወድቅ የዘመመን በእጅህ አቅንተህ አለህ አንተ የማዐዘን ድንጋይ እራስ ሆነህ አለህ አንተ ጉልበተኛ ሞቶ ሊገፋው ቡሞክር ባንተ ሃይሉ ከንቱ ሆኖ አየሁት ሲያፍር ለደሃደግ ወዳጅ ለተገፋው አዛኝ እኔስ እንደ አንተ ፈፅሞ አላየሁም/4 አይደለህም እንደሰው አይደለህም ጌታዬ አይደለህም እንደሰው አይደለህም አምላኬ አንተ የተቀጠቀጠውን ሸንበቆ አትሰብርም አንተ የተጎዳውን ልብ ዝም ብለህ አታልፍም አንተ በሃሜት በወሬ ውስጡ ለደቀቀ አንተ ትጠግነዋለህ አድርገህ ሌላ ሰው ከጥንት የምትሰራ ድንቅ ነው ልማድህ ደመና ቀደህ ትወርዳለህ ፈጣን ነህ እኔን ለመርዳት/2 አይደለህም እንደሰው አይደለህም ጌታዬ አይደለህም እንደሰው አይደለህም አምላኬ አንተ ከሰፈር መንደሩ ወቶ ለተገለለ አንተ በቃ የሱ ነገር ሞቷል የተባለ አንተ ያለፈውን ችግር ሁሉ አስረስተኸው አንተ በመካራው ሃገር ይኸው አፈራኸው ደለደልከው ያንን ተራራ አወጣኸኝ ከዛ መከራ ለውጥከው አንተ ኑሮዬን ዛሬን አይሁኝ ጌታዬ ደለደልከው ያንን ተራራ አወጣኸኝ ከዛ መከራ ተለወጠ ባንተ ኑሮዬ ተመስገንልኝ ጌታዬ ደግሞ ልቤ አርፎ ተደላድሎ ይኖራል አንተን ተስፋ ያደርጋል ከፊትለፊቴ ቆሞ ያስለቀሰኝ ተራራ ሁሌ ይምስለኝ ነበር የሚፈርስ በተራ አንተ ግን ከሰማይ ቃልህን ስትልከው ትልቁን ተራራ በአንዴ ነቀልከው ከስሩ ነቀልከው አይደለህም እንደሰው አይደለህም ጌታዬ አይደለህም እንደሰው አይደለህም አምላኬ

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play

More songs by Dagmawi Tilahun

See all 62 songs by Dagmawi Tilahun