Gubae

እረኛዬ

Ere%C3%B1ayie

ዮሐንስ ግርማ · እረኛዬ

Ere%C3%B1ayie is an Amharic mezmur (worship song) by Yohannes Girma, from the album Ereñayie.

እረኛዬ ማረፊያዬ ቃልክን ስትናገር ልብን ያሳርፋል የምትመክረው ምክር ተስፋን ያሳድራል ሆነህ አይቼሀለሁ ልቤ አንተን ወዶሀል /x2 አይከፋኝም አባ ለዚህ አትስጋ ምን ጎደለው አንተን የተጠጋ መተማመን መጓደድ ባንተ ነው ሁሉ ባለህ ሁሉን በፈጠርከው አይኖችህ በምድር ላይ ያያሉ ከእኔው ጋራ ይንከራተታሉ ሆድ ሲብሰኝ ከላይ ትወርዳለህ በደመናት ትረማመዳለህ እረኛዬ... ማይናወጥ ፀንቶ የሚኖረው ሰላም ደስታ ነፍሴን ሚመግበው መቼ በቁስ በመብል ወርቅ ሆነ በሚጠፉ መቼ እንዲህ ታጀበ ሲከናወን ቤት ጓዳ ሲሞላ ኑሮ ሲተርፍ ለአፈር ሲደላ አይደል በዚህ ደስታዬ ባንተ ነው ጠፊ ነገር ሊያጠፋኝ አይከጅልም እረኛዬ... የገባከውን ቃል ኪዳን አትረሳም የሰጠኸውን ተስፋ አታጠፋም ሌት እና ቀን ሁሌ ትተጋለህ እንዲፈፀም ቀኑን ታፈጥናለህ ይህን ላደርግ ሀይሌ እንዲህ አነሰ ብለህ አትመጣ ጉልበቴ ደከመ ባንተው ምለህ መች እንዲህ ይሆናል ችሎታህም ሁሌ ያስተማምናል እረኛዬ... ልቤ በሰው መቼም አይመካም ምደገፈው ፈራሽ አልጠጋም አይኑ በሰው በሟቹ ያረፈ እሱ ሲሞት ተስፋውም አረፈ ድንገት አርፈህ መርዶ አይነገር መንግስት ከአንተ ለሌላ አይሻገር በጉልበትህ ፅናት ትሄዳለህ ለዘላለም ንጉስ ትባላለህ እረኛዬ...

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play

More songs by Yohannes Girma

See all 19 songs by Yohannes Girma