Gubae

ድል በድል ጐዳና

Del Bedel Godana

ደረጀ ከበደ · ስብስብ

Del Bedel Godana is an Amharic mezmur (worship song) by Dereje Kebede, from the album Sebseb.

አዝ፦ ድል ፡ በድል ፡ ጐዳና (፪x) ክርስቲያን ፡ አሸነፈ ፡ ኢየሱስ ፡ አለውና (፪x) ያን ድቅድቅ ጨለማ የሞትን ሸለቆ ታገለው ክርስቲያን የእምነት ትጥቁን ታጥቆ አሻፈረኝ ብሎ ለእርሱ ላይረታ በድል ጥሎት ወጣ በጌታው መከታ አዝ:- ድል በድል ጎዳና ድል በድል ጎዳና ክርስቲያን ፡ አሸነፈ ፡ ኢየሱስ ፡ አለውና (፪x) የጥሻው ጨለማ ብርሃን ወጣበት ክርስቲያን በእምነት ሰይፍ አንዴ ቢዘምትበት የማጥመጃው ሜዳ በደም አጥለቅልቆ ሕያው ዘር ዘራበት እንዲበቅል አውቆ አዝ:-ድል በድል ጎዳና ድል በድል ጎዳና ክርስቲያን ፡ አሸነፈ ፡ ኢየሱስ ፡ አለውና (፪x) ጋሻ ጦሩ መንፈስ ፍላጻው እምነቱ ማን ሊቋቋመው ነው ያን ክንደ ብርቱ ሊያጠምዱት ሊያስቀሩት አጥብቀው ቢጥሩ ከአምላኩ ደም ቅጥር አልነቀለም እግሩን አዝ:-ድል በድል ጎዳና ድል በድል ጎዳና ክርስቲያን ፡ አሸነፈ ፡ ኢየሱስ ፡ አለውና (፪x)

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play

More songs by Dereje Kebede

See all 72 songs by Dereje Kebede