Gubae

ታማኝ ነው

Tamagn New

ዳዊት ሽመልስ · የእኔ አምላክ ይለያል · 2005

Tamagn New is an Amharic mezmur (worship song) by Dawit Shimeles, from the album Yeeniye Amlak Yileyal (2005).

አዝ ፦ ታማኝ ነው እግዚአብሔር መቼ ሰው ይጥላል ማንንም አይንቅም ደርሶ ይታደጋል በእውነት ለታመኑት እርሱን ለተጠጋ ያወጣል ጌታዬ ከጠላት መንጋጋ ወላጅ አልባን አሳዳጊ የተጣለውን ፈላጊ ስለጠላቱ የሞተ ብቻውን ድንቅን አድራጊ የጠፋውን ሰው መልሷል የስንቱን ሸክም አራግፏል በምድረበዳ ተገኝቶ ከአለት ውስጥ ምንጭን ያፈልቃል አዝ ፦ ታማኝ ነው እግዚአብሔር መቼ ሰው ይጥላል ማንንም አይንቅም ደርሶ ይታደጋል በእውነት ለታመኑት እርሱን ለተጠጋ ያወጣል ጌታዬ ከጠላት መንጋጋ ፍቅሩ ከሞት ውስጥ ያወጣል በቅንነቱ ይመራል ለተጠማ ከህይወት ውኃ በነጻ እንዲሁ ይሰጣል ለቸርነቱ ልክ የለው አይቋረጥ ልግስናው አንድ ቀን ጎድሎበት አያውቅ አምላኬ ሁሌ ሙሉ ነው አዝ ፦ ታማኝ ነው እግዚአብሔር መቼ ሰው ይጥላል ማንንም አይንቅም ደርሶ ይታደጋል በእውነት ለታመኑት እርሱን ለተጠጋ ያወጣል ጌታዬ ከጠላት መንጋጋ ታማኝነቱ ብዙ ነው ቃልኪዳኑንም ያከብራል እንደተነገረ የሚያደርግ እንደ እግዚአብሔር የት ይገኛል በማንም አይገመትም ሳይነግሩት የልብን ያውቃል የእስረኛውን ወጥመድ ሰብሮ በከፍታ ላይ ያኖራል አዝ ፦ ታማኝ ነው እግዚአብሔር መቼ ሰው ይጥላል ማንንም አይንቅም ደርሶ ይታደጋል በእውነት ለታመኑት እርሱን ለተጠጋ ያወጣል ጌታዬ ከጠላት መንጋጋ ፍቅሩ ከሞት ውስጥ ያወጣል በቅንነቱ ይመራል ለተጠማ ከህይወት ውኃ በነጻ እንዲሁ ይሰጣል ለቸርነቱ ልክ የለው አይቋረጥ ልግስናው አንድ ቀን ጎድሎበት አያውቅ አምላኬ ሁሌ ሙሉ ነው አዝ ፦ ታማኝ ነው እግዚአብሔር መቼ ሰው ይጥላል ማንንም አይንቅም ደርሶ ይታደጋል በእውነት ለታመኑት እርሱን ለተጠጋ ያወጣል ጌታዬ ከጠላት መንጋጋ

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play